የአዲስ ቻምበር ፕረዚደንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ በኳታር፣ በኢራን እና በየመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፈይሰል አሊይ ኢብራሂም ጋር በንግድን ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ዙርያ ተወያዩ፡፡

አዲስ ቻምበር ፤ ነሀሴ 25 ቀን 2018፡ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት / አዲስ ቻምበር በኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት፤ የገቢና ወጪ ንግድ እንዲፋጠን እንዲሁም የአገር ውስጥ ንግድ ተወዳዳሪ እንዲሆን በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ኢምባሲዎችና ተባባሪ አካላት ጋር አብሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የአዲስ ቻምበር ፕረዚደንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ በኳታር፣ በኢራን እና በየመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፈይሰል አሊይ ኢብራሂም ጋር በንግድን ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ዙርያ ውጤታማ የሆነ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል የተጠናከረ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲፈጠር፤ በሁለቱ ሀገራት የሚገኙ ባለ ሀብቶችን በማስተሳሰር ኤምባሲዎችና እንደ አዲስ ቻምበር የመሳሰሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ትልቁን ድርሻ መወጣት አለባቸው ብለዋል ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ በምክክራቸው፡፡

በኳታር የሚገኙ ባለ ሀብቶች በኢትዮጵያ የሚገኘውን መልካም የኢንቨስትመንት እድል ተጠቅመው ኢንቨስት በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይም መክረዋል፡፡

አዲስ ቻምበር የግሉ ዘርፍ ድምጽ!