የኢትዮ - ቤኔሉክስ ቢዝነስ ፎረም ዛሬ በሉግዘምበርግ በይፋ ተከፈተ። 

የኢትዮ – ቤኔሉክስ ቢዝነስ ፎረም ዛሬ በሉግዘምበርግ በይፋ ተከፈተ።

 

አዲስ ቻምበርና አባል ኩባንያዎቹ እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

 

የቢዝነስ ፎረሙ መንግስት እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች፣ ባለሀብቶች፣ የንግድ ምክር ቤቶች እና የልማት አጋሮችን በማገናኘት  የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር፣ የB2B ተሳትፎን ለማመቻቸት እና በኢትዮጵያ እና በቤኔሉክስ ሀገራት መካከል አዳዲስ የቢዝነስ እድሎችን ፈትሾ ለጋራ   ተጠቃሚነት ለመስራት ጉልህ ሚና ያለው መድረክ ነው።

 

በቢዝነስ ፎረሙ ከ20 በላይ የአዲስ ቻምበር ኩባንያዎች በመሳተፍ በኢትዮጵያ ቁልፍ የልማት ዘርፎች እያደገ ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጭ እያሳዩ ነው።

 

በሉክሰምበርግ የንግድ ምክር ቤት የአለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር Cindy Tereba; በኢትዮጵያ የሉክሰምበርግ አምባሳደር ክብርት Jeanne Crauser፤ በቤልጂየም፣ ሉክሰምበርግ፣ ኔዘርላንድስ እና በአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር እሸቴ ጥላሁን፤ እና የCBL-ACP ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት Mr.  Dominiek Viaene በመድረኩ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ንግግር አድርገዋል።

 

አምባሳደር እሸቴ በንግግራቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የገበያ ነፃነት እና በግሉ ሴክተር የሚመራ ኢኮኖሚ ሽግግር የኢትዮጵያን ጠንካራ የኢኮኖሚ ለውጥ እና እያደገ የመጣውን የኢንቨስትመንት አቅም የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል።

 

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን ቁፋሮ፣ በአይሲቲ፣ በታዳሽ ኃይል፣ በቱሪዝም፣ በጤና አጠባበቅ እና በሎጂስቲክስ እምቅ ኃብቶች የውጭ ኢንቨስተሮች በስፋት እንዲሳተፉ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

 

አክለውም ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ገበያዎች መግቢያ በር በመሆን በዋና ዋና የመሠረተ-ልማት  ግንባታ፣ የተሻሻለ የኢንቨስትመንት ሁኔታ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሚመራው የንፁህ ኢነርጂ መስፋፋት ስለምትጠቀም የኢኮኖሚው እድገት እርምጃ  ስትራቴጂካዊ ምሳሌ እንደሆነች ጠቁመዋል።

 

የሉክሰምበርግ እና የቤኔሉክስ ባለሀብቶች እያደጉ ያሉትን እድሎች ተጠቅመው ከኢትዮጵያ ጋር የረዥም ጊዜ ዘላቂ አጋርነት እንዲገነቡም ጥሪ አቅርበዋል።

 

በዛሬው እለት በሉክሰምበርግ የተከፈተው የኢትዮጵያ- ቤኔሉክስ የቢዝነስ ፎረም ከሜይ 19 እስከ ሜይ 22 ቀን 2026 ዓ.ም. በብራሰልስ ከተማ ይቀጥላል።

 

ምንጭ

 

MFAEthiopia Amharic  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

wpChatIcon
wpChatIcon