በ32 አክሲዮን ማህበራት ስር የተደራጁ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የመልሶ ማልማት ጥያቄ ምላሽ አገኘ፡፡
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የነጋዴው መብትና ጥቅም እንዲከበርና ተወዳዳሪነቱ እንዲጨምር ላበረከተው አስተዋጾ ከአዲስ አበባ አክሲዮን ህብረት ምስጋና ተችሮታል፡፡
(አዲስ ቻምበር፤ ግንቦት 7 2018 አ.ም) በአዲስ አበባ በተለይም በአዲስ ከተማ ፤ በንፋስ ስልክ ላፍቶና በየካ ክ/ከተሞች የሚገኙ 32 ትላልቅ የአክሲዮን ህብረት ቀደም ሲል ሲሰሩበት በነበረበት ቦታ በዘመናዊ አቅም ለማልማት ለከተማ አስተዳድሩ ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፡፡
የአዲስ አበባ አክሲዮን ህብረት ከ23 አመታት በላይ ሲያቀርብ የነበረው የሊዝ መሬት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ማግኘቱን ተከትሎ እንደሆነ የህብረቱ ኃላፊ አቶ ዘውዱ ግዛው በኢሊሊ ሆቴል በተዘጋጀው የምስጋና ፕሮግራም መርኀ ግብር ላይ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የምስጋና ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ቻምበር ፕረዚደንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግዱ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ ላበረከቱት አስተዋጾ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ በንግዱ ማህበረሰብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በንግድ ምክር ቤት ጥላ ስር የታቀፉ ነጋዴዎች አሁን ላይ የሚያነሱት ንግድ ነክ ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ እንደሆነ የገለጹት ወ/ሮ ዘሀራ የመርካቶ ነጋዴዎች ያቀረቡትን ጥያቄና ምላሽ እንደ አንድ ምሳሌ በማቅረብ አሁንም ቢሆን አባል ያልሆኑ ነጋዴዎች አባል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ንግድ ምክር ቤቱ አሁንም ቢሆን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የንግዱን ማህበረሰብ መብትና ጥቅም ለማስከበር ከመንግስትና ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
በዚህ መርኃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ አክሲዮኖች ህብረት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ አስተዋጾ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች ለከተማው ንግድ ቢሮ፤ ለአዲስ ቻምበር፤ ለአዲስ አበባ መሬት ልማት አስተዳደር፤ ለአዲስ ከተማ ክ/ከተማ እና ለተወሰኑ ግለሰቦች ምስጋና ተችረዋል፡፡
አንዱ አክሲዮን በውስጡ ከ200 እስከ 800 የንግድ ማህበረሰብ አባላት እንዳሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡
አዲስ ቻምበር የንግዱ ማህበረሰብ አገልጋይ!
