አዲስ ቻምበር በቅርቡ ተግባራዊ ለሚያደርገው የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ/ ኢአርፒ/ ቴክኖሎጂ ለማኔጅመንቱ የቅድመ ትግበራ ስልጠና እየሰጠ ነው፡ ፡

ንግድ ምክር ቤቱ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ የአሰራር ስርዓትን ተግባራዊ ማድረጉ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተ/ዋና ፀሃፊው አቶ ዘካሪያስ አሰፋ ስልጠናውን ሲከፍቱ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ በቅርቡ ተግባራዊ የሚያደርገው የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ የአሰራር ስርዓት አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችልና የተቋሙን አደረጃጀትና የስራ ፍሰት ለማስተካከል እንዲሁም የቴክኒክ ልህቀትን እውን ለማድረግ የሚያግዝ እንደሆነ በስልጠናው ላይ ተብራርቷል፡፡

በፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት በሚሰጠው ስልጠና የሁሉም የስራ ክፍል ሀላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተሳታፊ ናቸው፤ ፡

ይህ በቅርቡ ተግባራዊ የሚደርገው የኢአርፒ የአሰራር ስርዓት 13 የአፕሌኬሽን ሞጁሎች ያሉት ሲሆን የፋይናንስና ኮንትሮል፣ የሰው ሀብትና ፔሮል፣ የመረጃ ማዕከል፣ የንብረት አስተዳደርና ሎጀስቲክስ፣ የኢንተርፕራይዝ አሴት አስተዳደር፣ የጥሪ ማዕከል፣ ኮሚኒኬሽን እና ሁነት አስተዳደር፤የፕሮጀክት አስተዳደር እና የጥራት አስተዳደር፣ እንዲሁም ከአባላት ክፍያ ስብሰባ ጋር የተገናኙ ሞጁሎች በሁሉም የተቋሙ የስራ ክፍሎች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡

ይህን የአሰራር ስርአት ማስተግበር ንግድ ምክር ቤቱ እያካሄዳቸው ካሉ የለውጥ እንቅስቃሴዎች አንዱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡ ፡

ስልጠናው ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመላው ሰራተኛና ለአመራሮች በተከታታይነት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡ ፡