የፓኪስታን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሀሚድ አስጋር ካህን ከአዲስ ቻምበር ዋና ጸሃፊ ክንዳልም ዳምጤ ( ዶ/ር) ጋር ውይይት አካሄዱ::
ውይይታቸው በግሉ ዘርፍ እድገትና የጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር፡፡
ይህ የሆነው የአዲስ ቻምበር ዋና ጸሀፊ ክንዳለም ዳምጤ ( ዶ/ር) አዲስ አበባ ከሚገኘው የፓኪስታን ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ጋር በሸራተን ሆቴል በጋራ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የፓኪስታን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሀሚድን ጨምሮ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አጢፍ ሸሪፍ ፤ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችና የአዲስ ቻምበር የስራ ኃላፊዎች ተካፍለዋል፡፡
የምክክር መድረኩ በተለይም በኢትዮጵያና በፓኪስታን መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም ባህልን የማስተዋወቅ ስራ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን ሁለቱ ተቋማት (አዲስ ቻምበርና አዲስ አበባ የሚገኘው የፓኪስታን ኢምባሲ) በቀጣይ የየሀገራቱን የንግድ ልኡካን እንዲገናኙ በማድረግ የንግድ ትስስር በሚፈጠርበት ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር፡፡
ከቅርብ አመታት ወዲህ በኢትዮጵያና በፓኪስታን መካከል ያለው የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እያደገ የመጣ ሲሆን በተለይም አዲስ ቻምበርና አዲስ አበባ የሚገኘው የፓኪስታን ኤምባሲ ሚና ከፍተኛ ነው፡፡