በቅርቡ የተመረጡት የአዲስ ቻምበር የቦርድ አባላት ከቀድሞ የቦርድ አባላት ይፋዊ የስራ ርክክብ አደረጉ፡ ፡
በቅርቡ 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት /አዲስ ቻምበር/ አዲስ የመረጣቸው የቦርድ አባላት ከተሰናባቹ የቦርድ አባላት ጋር የስራ ርክክብ እንዲሁም ውይይት አካሂደዋል ፡ ፡
በዚህ መድረክ ላይ ተሰናባቾቹ የቦርድ አባላት ለምክር ቤቱ ስላበረከቱት ጉልህ ሚና ከአዳዲሶቹ አመራሮች ምስጋና ተችሯቸዋል ፡ ፡
የምክር ቤቱ ዋና ፀሃፊ ክንዳለም ዳምጤ/ ዶ/ር/ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ከዚህ ቀደም የነበሩ ክፍተቶችን በማረም ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡ ፡
ተወዳዳሪ የንግድ አውድ ባለበት አለም ምክር ቤቱንና የንግዱን ማህበረሰብ በፍቃደኝነት ለማገዝ በመቻላችሁ አዳዲሶቹን የቦርድ አባላት ምስጋና ይገባችዃል ብለዋል፡ ፡
ረጅም እድሜን ያስቆጠረው የንግድ ምክር ቤቱ ዘላቂ እንዲሆን የቦርድ አባላት ሚና ወሳኝ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን አሁንም በርካታ እድሎችና ተግዳሮቶች ከፊቱ እንዳሉና የምክር ቤቱ የቦርድ አባላት ብዙ ስራ እንደሚጠበቅባቸው የገለጹት ተሰናባቿ የቦርድ ፕረዚደንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ናቸው፡ ፡
በተመሳሳይ አዲሷ የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ በበኩላቸው የንግድ ምክር ቤቱን የቀደመ ስሙን ለመመለስ የሚታዩና የሚጨበጡ ስራዎችን ሰርቶ ለማለፍ ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል፡ ፡
በቀጣይም አዳዲስ የተመረጡ የቦርድ አባላት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ጠንካራና ተወዳዳሪ ምክር ቤት እንዲፈጠር የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ፡ ፡
በሪፎርም ሂደት ውስጥ የሚገኘው አዲስ ቻምበር በቀጣይ ከባለድርሻ አካላትና ከተለያዩ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር በአዲስና በዘመናዊ አስተሳሰብ በመቃኘት ቀጣይ የምክር ቤቱን እና የንግድ ማህበረሰቡን አቅም ማጠናከር እንደሚገባ ወ/ሮ ዘሀራ በርክክብ ስነስርአቱ ላይ ተናግረዋል፡፡
በስነስርአቱ ላይ የንግድ ምክር ቤቱ የምርጫ አመቻች ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል፡ ፡
