ከሁሉም ክልሎች የተውጣጣ የሰላምና የሽምግልና ልዑክ መቀሌ ገባ፤፤

ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌ አባገዳዎችና ሐዳሲንቄዎች ፣የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮችና የትግራይ ተወላጅ ነጋዴዎች ለሽምግልና እንዲሁም ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መቀሌ ተጉዘዋል፡ ፤

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ/ዶ/ር/ ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ከንግድ ማህበረሰብ የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች፣ ሐደሲንቄዎች እና የትግራይ ተወላጅ ነጋዴዎች ለሽምግልና መቀሌ የተገኙ ሲሆን በጉዟቸው 40 ሚልየን ብር የሚገመት ድጋፍ አሰባስበው ለሚመለከታቸው አስረክበዋል፡ ፡

ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የሰላምና የሽምግልና ልዑክ ከክልሉ አመራሮች ጋር በሰላም እና በቀጣይ ድጋፍ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ መክረዋል ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት /አዲስ ቻምበር/ ማህበራዊ ሀላፊነቱን ከመወጣት አንፃር ለተፈናቃይ ወገኖቻችን የሚሆን የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች አበርክቷል፡ ፤

የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ የሰላም ልኡኩ አካል በመሆን በሽምግልና እና  ድጋፉን በማበርከት ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡ ፡