የቢዝነስ ሥራ መሪዎችንና ሥራ ፈጣሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2016(ኢዜአ)፦ የቢዝነስ ሥራ መሪዎችንና ሥራ ፈጣሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ገለጸ።
የልምድ ልውውጥ መድረኩ “የሥራ መሪዎች መድረክ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ሲሆን አዲስ የመማማሪያ፣ የልምድ ልውውጥና የግንኙነት መረብ ማዳበር ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ፀሐፊ ዘካርያስ አሰፋ፤ በመድረኩ ላይ በርከት ያሉ የቢዝነስ ሥራ መሪዎችንና ሥራ ፈጣሪዎች የሚሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል።
የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ በሚጀመረው መድረክ የታላላቅ ቢዝነስ አንቀሳቃሾች የዘርፉን ፈተናዎችና ምርጥ ተሞክሯቸውን እንደሚያጋሩ ጠቁመዋል።
የኤስኤኬ የሥልጠና እና ማማከር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አደራ አብደላ፤ የመድረኩ አላማ ታላላቅ የሥራ መሪዎች ለወጣቶች የካበተ ልምዳቸውን በማካፈል ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው ብለዋል።
የመድረኩ አዘጋጆች የዓላማው ደጋፊ፣ የሥራ መሪ፣ የንግድ አከናዋኞችና የሥራ ፈጣሪዎች የመድረኩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
መረጃዎቻችንን፦
በቴሌግራም፡- https://t.me/EthiopianNewsA
በድረገጽ፡- https://www.ena.et/
የኢዜአ ዜናዎችን በአጭር የስልክ መልዕክት ለማግኘት፡- 9111
ፈረንሳይኛ ድረ-ገጽ https://www.ena.et/web/fre
አረብኛ ድረ-ገጽ https://www.ena.et/web/ara