አዲስ አውቶሞቲቭ ንግድ ትርኢት እና ኤክስፖ በኢግዚብሽን ማዕከል ተከፈተ

በአዲስ አበባ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የተዘጋጀውን  ንግድ ትርኢት የከፈቱት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጃንጥራር አባይ ናቸው፡፡

በመክፈቻ ስነስርአቱ የአዲስ አበባ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላት ፡ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ ለማወቅ ፍላጎት ያላቸው ጎብኝዎች ተገኝተዋል፡፡

ለአካባቢ ተስማሚ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪቃል በተዘጋጀው ንግድ ትርኢት  አምራቾች ፡ አስመጭዎች፡ ገጣጣሚዎች እንዲሁም ሌሎች በአውቶሞቲቭ ዘርፍ የተሰማሩ ተሳትፈውበታል፡፡ንግድ ትርኢቱ ለአምስት ቀን እንደሚቆይም ተጠቁሟል፡፡

wpChatIcon
wpChatIcon