የአዲስ አበባ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ኢንጂነር አበበ ጉርሜሳን ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ 

የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቱ ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው 17ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ኢንጀነር አበበን ጉርሜሳን ፕሬዚዳንት፤ አቶ አይችሉህም ከበደን ምክትል ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ዘጠኝ የቦርድ አባላትን በመምረጥ ተጠናቋል፡ ፡

በዕለቱ ከተመረጡት መካከል ኢንጀነር አበበ ጉርሜሳ ፣ አቶ አይችሉህም ከበደ ፣ አቶ ተሰፋየ ገ/ኪዳን እና ወ/ሮ ግሩምነሽ ይመር በቀጥታ የዘርፍ ምክር ቤቱን በመወከል የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር/ ላይ የቦርድ አባላት ይሆናሉ ተብሏል ፡፡

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት የአምራች ኢንዱስትሪው የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀው እንደ ዘርፍ ማህበራት ያሉ አደረጃጀቶች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል፡ ፡

የዘርፍ ምክር ቤቱን በቀጣይ ለሁለት አመታት እንዲመሩ የተመረጡት ኢንጅነር አበበ ጎርሜሳ ከተመረጡ በኃላ ባደረጉት ንግግር የአምራች ዘርፉ የስራ የስራ አጥነትን በመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፆ እያበረከተ መሆኑን ገልፀው የአምራች ዘርፉን ችግሮች ለመቀነስ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል ፡፡

ሆኖም ይህንን ችግር ለመቅርፍ ቦርዱ የሚያደርገውን እንቅሰቃሴ ሁሉም የዘርፍ ኢንዱስትሪው አባላት አብረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

ተሰናባቹ የአዲስ አበባ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አቶ ፋሲካው ሲሳይ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ኢንጅነር አበበ ጉርሜሳን እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል ፡፡

አክለውም ሁሉንም የቦርድ አባላት ትለቅ ሀላፊነት እንዳላባቸው ጠቅሰው ለተመረጡበት ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ያማከለ ስራ እንዲሰሩ አደራ ብለዋል ፡፡

ዘርፍ ምክር ቤቱ ጠንካራ እና በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞጋች እንዲሆን መሰራት አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በጉባኤው ላይ በክብር እንግድነት ከተገኙት መካከል የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ እና የቦርድ አባሉ ኢንጂነር አለማየሁ ንጋቱ ይገኙበታል፡ ፡

ፕሬዚዳንት መሰንበት እንደተናገሩት አምራች ከሌለ ነጋዴ የለምና ለአምራች ዘርፉ ልዩ ትኩረትና እገዛ ከባለድርሻ አካላት ያሻል ሲሉ አጽእኖት ሰጥተዋል፡ ፡

የአዲስ ቻምበር የቦርድ አባል ኢንጂ አለማየሁ ንጋቱ በበኩላቸው የዘርፍ ምክር ቤቱም ሆነ አዲስ ቻምበር አባላቶቻቸውን በእጅጉ በማስፋት ጠቃሚ የንግድ ድጋፍ አገልግሎቶችን መስጠት እንዳለባቸው ተናግረው ሁሉም ንግድ ምክር ቤቶች ለሀገር እድገት በማሰብ ተባብረው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡ ፡

ዘርፍ ምክር ቤቱ በካሄደው 17ተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የ2016 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፖርት፣ የ2016 የውጭ ኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበት በመሉ ድምፅ ፅድቋል ፡፡

wpChatIcon
wpChatIcon