በአዲስ አበባ  እና በዱባይ መካከል ስትራቴጂካዊ አጋርነትን መገንባት የሚያስችል የንግድ መድረክ ሊካሄድ ነው፡፡  

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት( አዲስ ቻምበር) ከዱባይ የንግድ ምክር ቤት ጋር በመተባበር (Dubai-Ethiopia Business Connect) የተሰኘ ታላቅ የንግድ ለንግድ መድረክ ግንቦት 14 ቀን 2018 አ.ም በሸራተን አዲስ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

 

 

ለአንድ ቀን የሚቆየው ይህ መድረክ ዱባይ ያላትን ዓለም አቀፍ የንግድ እና የሎጅስቲክስ ማዕከልነት በመጠቀም የኢትዮጵያን እያደገ የመጣውን የሸማቾች አቅም፣ የኢነርጂ ዘርፍ እና በማደግ ላይ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማጠናከር ያለመ ነው።

 

 

በዚህ መድረክ የሀገር ውስጥ ተሳታፊዎች ከታዋቂ የዱባይ ኩባንያዎች ጋር ቀጥተኛ የንግድ ትስስር መፍጠር፤ ወቅታዊ የገበያ ሁኔታዎችን እና እየታዩ ያሉ የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችን መረዳት፡ በልዩ የዲጂታል መድረክ አማካኝነት ከዱባይ ከሚመጡ የውሳኔ ሰጪ አካላት እና ባለሀብቶች ጋር ፊት ለፊት የመገናኘት እድል የሚኖረው ሲሆን በዚህ ጠቃሚ የንግድ መድረክ ላይ በመሳተፍ የንግድ ስራዎን ለማስፋፋትና አዳዲስ አጋሮችን ለማፍራት የሁለቱ ሀገራት የንግድ ምክር ቤቶች ጥሪ አቅርበዋል።

 

አዲስ ቻምበር የግሉ ዘርፍ አገልጋይ!

wpChatIcon
wpChatIcon