የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የቢዝነስ ኢኖቬሽን ማዕከል ቀጣይነት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ፡፡
የአዲስ ቻምበር አካል የሆነው የቢዝነስ ኢኖቬሽን ማዕከል ፕሮጀክት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2025 ካበቃ በኃላ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በምክር ቤቱ የማኔጀመንት አባላት ወይይት ተካሄዶበታል ፡፡
የምክር ቤቱ ዋና ፀሀፊ አቶ ሽበሺ ቤተማርያም ፕሮጀክቱ ማዕከሉን ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በርካታ እንቅሰቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
በተለይም ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ በኃላ ሊሰሩ ከታቀዱ ስራዎች መካከል አንዱ የቢዝነስ ኢኖቬሽን ማዕከሉን በገቢ ረገድ ራሱን በራሱ የሚደግፍ እንዲሆን ማድረግ ነው ብለዋል ፡፡
ለስራ ፈጣሪዎች ( ኢኖቬተርስ ) ሰልጠና እና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት ብሎም ከኢንቨሰተሩ ጋር ማገናኝት ከሚተግብራቸው አንዱ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
አክለውም የማዕከሉ ዓለማ ስራ መፍጠር የሚችሉ ወጣቶችን በመደገፍ አገር መቀየር መሆኑን ጠቅሰው ፤ በተለይ ከግዙፍ አገር በቀል ኩባንያዎች ጋር አብረን የምንሰራበትን ሁኔታ እያመቻቸን ነው ብለዋል ፡፡
በሀገሪቱ ከሚገኙ ግዙፍ ኮርፖሬሽኖች መካከል ፋይናንስ ተቋማት ጋር አብሮ ለመሰራት እንቅሰቃሴዎች መኖራቸውን ጨምረው ገልፀዋል ፡፡
የንግድ ምክር ቤቱ ምክትል ዋና ፀኃፊ አቶ ስዩም ጫኔ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ዘላቂ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ከአውሮፓ ህብረት ባገኝው ድጋፍ ለአራት አመት ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ እ. ኤ.አ በ2022 ስራ መጀመሩ ይታወሳል ፡፡
የቢዝነስ ኢኖቬሽን ማዕከል የቢሮ መገኛውን ሲኤምሲ በሚገኝው አዲስ አፍሪካ ኢግዚቢሽን እና ኮንቬንሽን ማዕከል ውስጥ አድርጓል ፡፡