የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱን የፍትሕና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ዕጩዎች ሹመት አጽድቋል፡፡
የቦርድ አባል ሆነው ከተሾሙት መካከል የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕረዚደንት ወ/ሮ ዘሃራ መሃመድ ይገኙበታል፡፡ ወ/ሮ ዘሀራ እንደ ቀይ መስቀል ፤ የመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ድርጅት በመሳሰሉት ተቋማት ውስጥ የቦርድ አባል መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ከወ/ሮ ዘሀራ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አቶ ሞገስ ባልቻ – የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ፤ ነብዩ ባዬ ፤ አቶ ሠለሞን ካሳ ፤ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንዲሁም ሚኤሳ ኤሌማ (ዶ/ር)-የሥራ አመራር ቦርድ አባል ሆነዉ መሾማቸውን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግባቧል፡፡
