የአዲስ ቻምበር አባል ድርጅቶች በ19ኛው የአዘርባይጃን አለምአቀፍ የግብርና፣ ምግብና መጠጥ አለምአቀፍ ኢግዚቢሽን (Caspian Agro Expo 2026) ላይ የተሳካ ተሳትፎ አድርገው ተመለሱ፡፡

እ.አ.አ. ከሜይ 5-8/2026 በአዘርባጀን ዋና ከተማ ባኩ በተካሄደው 19ኛው የአዘርባይጃን አለምአቀፍ የግብርና፣ ምግብና መጠጥ አለምአቀፍ ኤግዚቪሽን ላይ ከ7 ድርጅቶች የተውጣጡ 12 ተሳታፊዎች ምርትና አገልግሎታቸውን አስተዋውቀው እና የገበያ ትስስር ፈጥረው ተመልሰዋል፡፡

 

 

በዚህ ኤግዚቪሽን ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ፓቭሊዮን የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዲስ ቻምበር ያዘጋጀው የንግድ ልዑካን ቡድን በአፍሪካ ፓቪሊዮን ውስጥ ኢትዮጵያን ቡዝ በመያዝ ቡናን እና ሌሎች የግብርና ውጤቶችን ለእይታ አቅርቧል፣ በርካታ ጐብኝዎችንም አግኝቷል፡፡

 

 

ይህንን አለምአቀፍ ኤግዚቪሽን መርቀው የከፈቱት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት Ilham Aliyev ሲሆኑ፣ አፍሪካ በዚህ ኤግዚቪሽን ተሳታፊ በመሆኗ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው፣ በቀጣይ ጊዜ በመሰል ኤግዚቪሽኖች እና የቢዝነስ ግንኙነቶች ላይ በስፋት ለመሳተፍ ተዘጋጁ ብለዋል፡፡

 

 

በአጠቃላይ አዲስ ቻምበር ያዘጋጀው የንግድ ልዑካን ቡድን በአዘርባይጃን የግብርና፣ ምግብ እና መጠጥ አለምአቀፍ ኤክስፖ የነበረው ተሳትፎ ከፍተኛ ቦታ የተሰጠውና ከአዘርባይጃን እና ሌሎች ተሳታፊ ሀገራት ከመጡ አቻዎች ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ ውይይቶች እና ስምምነቶች የተፈረሙበት የቢዝነስ መድረክ እንደነበር ከተሳታፊዎች መረዳት ተችሏል፡፡

 

 

በአዘርባጃን በኩልም፣ ኢትዮጵያውያን ከሜዲካል ቱሪዝም አንፃር አብረው እንዲሰሩ፣ ከትልልቅ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ጋር በማልማትም ሆነ የለሙትን በመግዛት አብረው እንዲሰሩ፣ እንዲሁም በትልልቅ ዩኒቨርሲቲዎች የስኮላርሽፕ ዕድሎች እንዳሉ ተገልጿል፡፡

wpChatIcon
wpChatIcon