አዲስ ቻምበር እና የሔናን (ቻይና) ንግድ ም/ቤት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

በይድነቃቸው ዓለማየሁ
በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሠነድ በንግድ ማስፋፊያ፤፤በገበያ መረጃ ልውውጥ እና በኢንቨስትመንት መስኮች በጋራ ይሰራሉ፡፡
በተጨማሪም በግብር፤በቀረጥ ፤በንግድ ሥራ አመራር ፤ በንግድ ፖሊሲዎች እና ሕግጋት ዙሪያ የምክክር መድረኮችን ያዘጋጃሉ፡፡
የአዲስ ቻምበር ፕሬዝደንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ንግድ ም/ቤቱ ቀደም ሲል ከበርካታ ተባባሪ አካላት ጋር ስምምነቶችን ማድረጉን ገልጸው ፤ለሔናን ንግድ ምክር ቤት አባላት አስፈላጊውን እገዛ እና ትብብር ያደርጋል ብለዋል፡፡
በተለይ የሁለቱም ንግድ ምክር ቤቶች የአቅም ግንባታ ፤ የልምድ ልውውጥ እና የቢዝነስ ግንኙቶችን እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የሔናን -ኢትዮጵያ ንግድ ም/ቤት ተወካይ ሚ/ር ቶኒ ዣንግ በበኩላቸው በሔናን የሚገኙ ኩባንያዎች በንግድ፤ በኮንስትራክሽንና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ለመሳተፍ ፍላጎት አላቸው ብለዋል፡፡
ስምምነቱ የሁለቱንም ንግድ ም/ቤት አባላት ግንኙነት የበለጠ አንደሚያጠናክረው እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ ቻምበር ዋና ጸሐፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያም በበኩላቸው የምክር ቤቱን ሠራተኞች ሰልጠና አንዲሰጡ አንዲሁም ለ ERP ፕሮግራም የመሣሪያዎች ድጋፍ አንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡