የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ምክር ቤቱን እንዲመሩ የተመረጡት አዲሷ ፕሬዚደንት ወ/ሮ ዛህራ መሀመድ ከምክር ቤቱ የቀድሞ ፕሬዚደንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡
በርክክብ ስነስረሃቱ ላይ አዲሱ ም/ፕሬዘዳንት ኢንጂነር አበበ ጉርሜሳና የዴሬክተሮች ቦርድ አባል ወ/ሮ ሳራ ሰለሞን እንዲሁም ከአዲስ አበባና ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች የተወከሉ የ/ጽቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ወ/ሮ ዛህራ መሀመድን የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አድርጎ መምረጡ ይታወቃል፡፡