የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ንግድ ቢሮ ከአዲስ ቻምበር እና ከሸማቹ ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ መስራቱ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና የሸማቾች ጥበቃ ማህበር አመራሮች ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር ተቀራርበው በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት አካሂደዋል፡፡

አዲስ ቻምበር የ2018 ዓ.ም የስራ አፈጻጸምሙን አስመልክቶ ከንግድ ቢሮ ጋር ሰፈ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡ ምክርቤቱ በተገባደደው በጀት ዓመት ጠንካራ አፈጻጸም ማሳየቱ ተጠቁሟል፡፡

በውይይቱ ማህበራቱ የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ በሰሯቸው ስራዎች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ተችሏል።

የንግድ ስርዓቱን ምቹ ለማድረግም የአዲስ ቻምበር እንዲሁም የሸማቾች ጥበቃ ማህበር አመራሮች ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡