ኢትዮጵያ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀውን የተበታተነ የንግድ አስተዳደር ሥርዓት ለመቀየርና ለላኪዎች፣ አስመጪዎችና ባለሀብቶች ግልጽና ሊተነበይ የሚችል አሠራር ለመፍጠር የሚያስችላትን የመጀመሪያውን ብሔራዊ የንግድ ፖሊሲ አጸደቀች።
በተጠናቀቀው ሳምንት በሚኒስትሮች ምክርቤት የጸደቀው ይህ ፖሊሲ፣ ለበርካታ አስርት ዓመታት የሀገሪቱን የንግድ ዘርፍ ተወዳዳሪነት ሲያዳክሙና ለብልሹ አሠራር በር ሲከፍቱ የቆዩትን እርስ በርሳቸው የሚጋጩ መመሪያዎችንና አሠራሮችን ሙሉ በሙሉ የሚተካ ነው።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ እንደገለጹት፣ አዲሱ ማዕቀፍ በተደጋጋሚ ለሚቀያየሩ መመሪያዎች እውቅና የማይሰጥ በመሆኑ በንግድ ቁጥጥር ሥርዓቱ ላይ መረጋጋት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያሰፍናል።
ፖሊሲው የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከለመደው ያልተቀነባበሩ የግብርና ምርቶች ኤክስፖርት ጥገኝነት በማውጣት፣ ወደ ማኑፋክቸሪንግ፣ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶች፣ አገልግሎቶችና ቱሪዝም ዘርፎች ላይ እንዲያተኩር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የንግድ ልማት አገልግሎትና ፖሊሲ ጥበቃ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ካሳሁን ማሞ፣ ምክር ቤቱ እንዲህ ዓይነት ሁሉን አቀፍ ፖሊሲ እንዲወጣ ለረጅም ጊዜ ሲወተውት እንደነበር አስታውሰዋል። ፖሊሲው የግል ባለሀብቱ በልበ ሙሉነት እንዲያቅድና ኢንቨስት እንዲያደርግ የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ
Ethiopia approves first national trade policy after years of fragmentation
