አዲስ ቻምበር እና የቻይናው አለም አቀፍ የወጪ ንግድ ልማት ቢሮ በጋራ መስራት በሚችሉበት ዙሪያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ ።

አንጋፋው የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ከቻይና የንግድ ሚኒስቴር የወጪ ንግድ ልማት ቢሮ ጋር ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ተፈራርሟል ።

ስምምነቱ የሁለቱን ሐገራት የንግድ ልውውጥ የሚያሳድግና የኢትዮጵያ አምራቾች በቻይና ሰፊ ገበያ በቀላሉ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ የሚያመቻች ነው።

በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የንግድ ሚዛን ልዩነት ሰፊና ወደ ቻይና ያደላ ሲሆን ይህንን ልዩነት ለማጥበብ አዲስ ቻምበር ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል።

ስምምነቱን በአዲስ ቻምበር በኩል ዋና ፀሐፊው አቶ ዘካርያስ አሰፋ ፈርመውታል።

ሁለቱ አካላት በመተባበር ባለፈው ሳምንት ውጤታማ የሆነ የኢትዮ ቻይና የቢዝነስ ኮንፈረንስ እና የንግድ ለንግድ ግንኙነት በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል ማከናወናቸው ይታወሳል ።

#አዲስ ቻምበር