በርካታ ሃገራትን ያሳተፈው የአፍሪካ ሼርድ ቫልዩ እንዲሁም የ ESG ጉባኤ በኬንያ ናይሮቢ ተካሄደ

በጉባኤው የአዲስ ቻምበርም ተሳታፊ ነበር
በእለቱ በቴክኖሎጂ እና በኮሙኒክሽን ዘርፍ የተሰማራው ሳፈሪኮም እና ሌሎች የንግድ ተቋማት ቀጣይነት ያላቸው የልማት ክንውኖቻቸውን አስመልክቶ ሪፖርት አቅርበዋል ፡፡
በተጨማሪም ወጣቶችን ሴቶችን እንዲሁም በዘላቂ የልማት ግቦች ትግበራ ዙርያ በርካታ የንግድ ተቋማት እና ባለሞያዎች ልምዶቻቸውን አካፍለዋል ፡፡
በጉባኤው የአፍሪካ ሃገራት ያላቸውን የተፈጥሮ እና የሰው ሃብት ከግምት በማስገባት ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት በቴክኖሎጂ፡በፋይናንስ እንዲሁም በማህበረሰብ ተኮር ስራዎች መደጋገፍ እና እራሳቸውንም ማብቃት እንደሚያስፈልጋቸው ተጠቁሟል፡፡
ለአፍሪካውያን ችግር መፍትሄ ከዜጎቿ እንጂ ከሌሎች መጠበቅ እንደሌለበት በተነሳበት ጉባኤ ላይ ወጣቶች እና ታዳጊዎች ትልቁን ድርሻ ሊወስዱ እና ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቷል፡፡
የዴንማርክ ኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን በምስራቅ አፍሪካ ከተለያዩ የቢዝነስ ማህበራትን ካቀፉ ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻዎች በአየር ንብረት በማህበራዊ እንዲሁም በአስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ቁጥራቸው ከ17 በላይ ባለድርሻዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ስልጠናው የንግድ ተቋማት ከቅርብ ግዜ ወዲህ በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረትን እየሳበ እና አስገዳጅ እሆነ የመጣውን የ ESG ማለትም የንግድ ተቋማት በስራ ሂደታቸው ለአየር ንብረት ለማህበረሰቡ እና በአስተዳደር ስራቸው ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ በሚያስችለው ጽንሰ ሃሳብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
By Senait Eshetu
wpChatIcon
wpChatIcon