የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት / አዲስ ቻምበር/ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ፤ የቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት የቤልጂየም አምባሳደር ሚስ አኔሊስ በሩሰልን ተቀብለው በንግድና ኢንቨስትመንት ማሳፋፋት ዙሪያ መክረዋል፡ ፡
ውይይታቸው በቀጣዩ ወር በአዲስ አበባ የሚካሄደውን ታላቅ የንግድ ኮንፈረንስ የተመለከተ እና በተለያዩ የቤልጂየም ከተሞች መካከል ያለውን የንግድ፣የገበያና የኢንቨስትመንት ትስስር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
ሁለቱ ተቋማት (አዲስ ቻምበርና አዲስ አበባ የሚገኘው የቤልጂየም ኢምባሲ በቀጣይ የንግዱ ሕብረተሰብን እርስ በእርስ ለማገናኘት፣ የንግድ ለንግድ ግንኙነት የሚፈጠርበት በአጠቃለይ የግሉን ዘርፍ ለማሳደግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በኢትዮጵያና በቤልጂየም መካከል ያለው የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እያደገ እና ቤልጂየም የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ መዳረሻ እየሆነች መምጣቷን ለማወቅ ተችሏል፡ ፡