14ኛው እርሻ ና የምግብ ዓለማቀፍ የንግድ ትርዒት በስኬት ተጠናቀቀ::

ለ3 ቀናት የተካሄደውና ከ70 በላይ የውጪና የአገር ውስጥ ኩባንያዎች የተሳፉበት የአዲስ ቻምበር የእርሻና የምግብ ዓለማቀፍ የንግድ ትርዒት በስኬት ተጠናቅቋል፡፡
በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው የመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ የአዲስ ቻምበር ፕሬዝደንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ባስተላለፉት መልዕከት አዲስ ቻምበር በየአመቱ 3 ንግድ ትርዒቶችን እንደሚያካሂድ አስታውሰው እኒህ ታላላቅ የንግድ ማስፋፊያ ሁነቶች በአገራችን ንግድና ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ትልቅ ድርሻ አላቸው ብለዋል፡፡
ዓለማቀፍ ንግድ ትርዒቶች የገበያ አማራጮችን ለማፈላለግ፤አዳዳስ የንግድ ሸሪኮችን ለማፍራት እንዲሁም ዘላቂ የንግድ ትስስሮችን ለመመስረት አይነተኛ መሣሪያዎች ናቸው ብለዋል፡፡
በስነሥርዓቱ ላይ ለተሳታፊ ኩባንያዎች ሽልማት የተሰጠ ሲሆን ትርዒቱ በሰኬት እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ ባለድርሻዎች ወ/ሮ መሰንበት ምስጋና አቅርበዋል፡፡