ንግድ ምክር ቤቱ  ለሴት የቢዝነስ መሪዎች በሥነ ጾታ ሥርዓት አተገባበር   ላይ ሥልጠና ሰጠ

በአገራችን ለሥርዓተ ጾታ የተሰጠው  የፖሊሲ ትኩረት፤ሴቶች በስራ ፈጠራ እና በንግድ ሰራ አመራርነት ማሳተፍ ያለው ሚና እና ሴት ስራ ፈጣሪዎችን እና አመራሮችን  ማሳደግ የሚቻልባቸው ስልቶች የሚሉት ነጥቦች  የስልጠናው ዓላማዎች  ናቸው፡፡

የአገራችን ሕብረተሰብ ለሴቶች የሚሰጠው የተዛባ ግምት ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ ነው፡፡

ይህም ሴቶች ለብዙ ማሕበራዊ፤ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅሞች ባይተዋር ሆነው አንደቆዩ ተወስቷል፡፡  ነገር ግን ከቅርብ አመታት ወዲህ በሕብረተሰቡ ዘንድ የቆየው አስተሳሰብ እየተቀየረ መጥቷል፡፡

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ጥሩ ጥሩ ፖሊሰዎቸ፤ሕግጋት እና የሥርዓተ ጾታ መመረያዎች ቢኖሩም ገና ብዙ መሥራት አለብን ይላሉ  ስልጠናውን  የሰጡት አቶ  መዝገቡ በላይ ፡፡

ጥናቶች አንደሚያሳዩት  በቢዝነሱ ዓለም የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ እርምጃ ከሚገድቡት ዋና ዋና ተግዳሮቶች መካከል፡ የገንዘብ ድጋፍ ማጣት; ውስብስብ የአስተዳደር ሂደቶች፤ ንግድ ለመጀመር  ኪሣራ ይከሰታል ብሎ መፍራት የሚሉት ይገኙበታል፡፡ በተለይም ኪሳራን መፍራት አስመለክቶ በቅርቡ የአውሮፓ ኮሚሽን ባወጣው ጥናት መሠረት  ኪሳራን መፍራት ሴቶች የራሳቸውን ሥራ(ቢዝነስ ) ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት ከሚገድቡ ትልልቅ እንቅፋቶች መካከል   43 በመቶ  ድርሻ ይይዛል ይላል፡፡

ሌላዋ አሰልጣኝ ወ/ሮ ወርቄ ሃይሉ  በበኩላቸው  በንግድ ሥራ (በቢዝነስ ኩባንያ)  አመራር  እና ውሳኔ ሰጪ ለመሆኑ የበቁ ሴቶች ቁጥር  ዛሬም አነስተኛ ነው፡፡

ዛሬ ላይ  በዓለም ከ500 ትላልቅ ኩባያዎች መካከል በሴቶች የሚመሩት በአማካይ  ከ 50 አይበልጥም ብለዋል፡፡

የፆታ እኩልነትን ለማጎልበትና ሴቶችን በኢኮኖሚና በአመራር ክህሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በንግድ ስራ አመራር ቦታዎች ላይ ሴቶችን በበቂ ሁኔታ ማሳተፍ ፤ በሴቶች ባለቤትነት የሚመሩ ድርጅቶች ስራቸውን በተሻለ መንገድ ማከናወን የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን መንደፍ እና በተገቢ መንገድ መተግበር፤ሴቶች ለተለያዩ ኩባንያዎች የቦርድ አባልና ሃላፊ እንዲሆኑ ማገዝ፤ ተቋማት ለፆታ እኩልነት ተጠያቂ እንዲሆኑ ተቋማዊ ፖሊሲ እና  አሰራሮች  መዘርጋት ያስፈልጋል የሚሉት ነጥቦች  በጥናቱ ከተሰነዘሩ ምክረ  ሃሳቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ንግድ ምክር ቤቱ  ለሴት የቢዝነስ መሪዎች በሥነ ጾታ ሥርዓት አተገባበር   ላይ ሥልጠና ሰጠ

በይድነቃቸው ዓለማየሁ

በአገራችን ለሥርዓተ ጾታ የተሰጠው  የፖሊሲ ትኩረት፤ሴቶች በስራ ፈጠራ እና በንግድ ሰራ አመራርነት ማሳተፍ ያለው ሚና እና ሴት ስራ ፈጣሪዎችን እና አመራሮችን  ማሳደግ የሚቻልባቸው ስልቶች የሚሉት ነጥቦች  የስልጠናው ዓላማዎች  ናቸው፡፡

የአገራችን ሕብረተሰብ ለሴቶች የሚሰጠው የተዛባ ግምት ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ ነው፡፡

ይህም ሴቶች ለብዙ ማሕበራዊ፤ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅሞች ባይተዋር ሆነው አንደቆዩ ተወስቷል፡፡  ነገር ግን ከቅርብ አመታት ወዲህ በሕብረተሰቡ ዘንድ የቆየው አስተሳሰብ እየተቀየረ መጥቷል፡፡

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ጥሩ ጥሩ ፖሊሰዎቸ፤ሕግጋት እና የሥርዓተ ጾታ መመረያዎች ቢኖሩም ገና ብዙ መሥራት አለብን ይላሉ  ስልጠናውን  የሰጡት አቶ  መዝገቡ በላይ ፡፡

ጥናቶች አንደሚያሳዩት  በቢዝነሱ ዓለም የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ እርምጃ ከሚገድቡት ዋና ዋና ተግዳሮቶች መካከል፡ የገንዘብ ድጋፍ ማጣት; ውስብስብ የአስተዳደር ሂደቶች፤ ንግድ ለመጀመር  ኪሣራ ይከሰታል ብሎ መፍራት የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በተለይም ኪሳራን መፍራት አስመለክቶ በቅርቡ የአውሮፓ ኮሚሽን ባወጣው ጥናት መሠረት  ኪሳራን መፍራት ሴቶች የራሳቸውን ሥራ(ቢዝነስ ) ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት ከሚገድቡ ትልልቅ እንቅፋቶች መካከል   43 በመቶ  ድርሻ ይይዛል ይላል፡፡