የአዲስ አፍሪካ ዓለምቀፍ የኤግዚቢሽንና ኮንቬንሽን ማዕከል በቀጣይ ሶስት ወራት ውስጥ ሥራ እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ የገና በዓል ኢግዚቢሽን እና ባዛር ለማሰተናገድ ዝግጀቴን እያጠናቀቅኩ ነው ብሏል ፡፡

የማዕከሉ ዋና ስራ አሰኪያጅ አቶ ሲሳይ ገመቹ ባደረጉት ገለፃ የኢግዚቢሽንና ኮንቬንሽን ማዕከሉ ከኢግዚቢሽን ማሳያ በተጨማሪ ሱቆች፣ ሬስቶራንቶች እንዲሁም አንፊ ቲያትር እና ደረጃውን የጠበቀ ፓርኪንግ አለው ብለዋል ፡፡ በዚህም የቁሳቁስ እና መገልገያ መሣሪያዎችን በማሟላት በቀጣይ 3 ወራት ውስጥ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለዋል፡፡ በታህሳሰ ወር ከሚከበረው የገና በዓል ጋር ተያይዞ የሚካሄዱ የፋሲካ እና ኢዳል ፈጥር ኢግዚቢሽኖች ተቀብሎ ለማሰተናገድ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑንም አቶ ሲሳይ ለጎብኝዎች ተናግረዋል ፡፡ የኢግዚቢሽን ማሳያው ቦታ ከፍታው እስከ 28 ሜትር ከፍታ ያለው መሆኑን የገለፁት አቶ ሲሳይ ፤ ይህም ሙቀትን ለመከላከል የሚያስችል ተፍጥሯዊ ማቀዝቀዥ እንዲኖርው ያስችለዋል ብለዋል፡፡ ከኢግዚቢሽን ማሳያ ቦታው በአንዴ እሰከ 4ሺ ሰዎችን እንዲሰበሰቡ የሚያስችል አዳራሽ እንዲሆን ታስቦ የተገነባ መሆኑን ገልፀዋል፡፡በጠጨማሪም ደረጃውን የጠበቀ ሳውንድ ሰርዓት ( ሲሰተም ) የተገጠመለት መሆኑን አቶ ሲሳይ ጨምረው ገልፀዋል ፡፡ በሶስት ምዕራፍ ተከፍሎ ግንባታው እየተካሄደ የሚገኝው የአዲስ አፍሪካ ኢግዚቢሽንና ኮንቬንሽን ማዕከል ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል የሚኖረው ሲሆን ፤ ለዚህም ግንባታቸው የተጠናቀቁ ሁለት መንታ ህንፃዎችን መግዛቱንም እንዲሁ ፤ የአዲስ አፍሪካ ኢግዚቢሽንና ኮንቬንሽን ማዕከል የግንባታ ፕሮጀክቱ በ2009 አ.ም መጀመሩን ያስታወሱት አቶ ሲሳይ ፤ይሁንናነ በተለያ ምክንያቶች በተያዘለት የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ አልቻለም ፡፡ የዋጋ ግሽበት፤በገንዘብ እጥረት ፣ የብረት ዋጋ መናር እንዲሁም የኮቪድ ወረርሽን ዋና ዋና ምክንያቶች ነበሩ ብዋል፡፡ ምንም እንኳን ፕሮጀክቱ ለረዥም ጊዜ ቢጓተትም መንግሥት በሰጠው አቅጣጫ እና የከተማ አስተዳደሩ በሰጠው አመራር በመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቅቋል ብለዋል ፡፡የአዲስ አፍሪቃ ዓለም ዓቀፍ ኤግዚቢሽንና አ,ኮንቬንሽን ማዕከል ሃሳብ ጠንሳሹ የአዲስ አበባ ንግድ ም/ቤት እንደነበር ይታወቃል ፡፡ ይሁንና ንግድ ምክር ቤቱ ብቻውን መገንባት ባለመቻሉ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት እየተገነባ ይገኛል ፡፡ ማዕከሉ አሁን ላይ 1ሺ52 ባለ አክሲዮኖች ያሉት ሲሆን የተከፈለ ካፒታሉም 5.5 ቢሊየን መድረሱ ለማወቅ ችለናል ፡፡

wpChatIcon
wpChatIcon