የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት / አዲስ ቻምበር ጠንካራና ተወዳዳሪ የግል ዘርፍ በኢትዮጵያ እንዲፈጠር ከመስራት ባለፈ የንግዱ ማህበረሰብና አባላቱ የኩባንያ ማህበራዊ ኃላፊነትን እንዲወጡ በተለይም በስራ እድል ፈጠራ፤ በድህነት ቅነሳና በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ወቅት ለዜጎች በመድረስ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል፡፡
በተለይም የንግዱ ማህበረሰብ በሰብአዊ ድጋፍ ዙርያ እንዲሰማራና የበኩሉን አስተዋጾ እንዲያደርግ ምክር ቤቱ ላበረከተው ከፍተኛ አበርክቶት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ለምክር ቤቱ እውቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር የሚያከናውናቸውን የሰብአዊ አገልግሎት ስራዎች ተደራሽ ለማድረግ ይረዳው ዘንድ በሚያደርገው የአባላት ቁጥር እንዲጨምርና ገቢ ማሰባሰብ ስራዎች ላይ የተጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ሰኞ ሰኔ 9 ቀን 2017 አ.ም በተካሄደው ፕሮግራም ላይ ተገልጿል፡፡