የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ የቬንዙዌላ አምባሳደርን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡ ፡

እኤአ ከሰኔ 5 – 6፣ 2025 የአዲስ ቻምበር አባል ኩባንያዎች በቬነዝዌላ ካራካስ ተገኝተው ከአቻዎቻቸው ጋር የንግድ ለንግድ ግንኙነት እንዲያካሂዱ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት / አዲስ ቻምበር/ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ፤ እና የማኔጅመንት አባላት የቬንዙዌላ አምባሳደር ሚስተር ኤዲ ጆሴ ኮርዶቫን ተቀብለው በንግድና ኢንቨስትመንት ማሳፋፋት ዙሪያ መክረዋል፡ ፡

ውይይታቸው በቀጣዩ ወር ጁን 5 እና 6 2025 በካራካስ  የሚካሄደውንና ከ20 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት ታላቅ የግብርና ንግድ ኤግዚብሽን የተመለከተ እና በተለያዩ የቬኔዙዌላ ከተሞች  መካከል ያለውን የንግድ፣የገበያና የኢንቨስትመንት ትስስር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።

ሁለቱ ተቋማት (አዲስ ቻምበርና አዲስ አበባ የሚገኘው የቬኔዙዌላ ኢምባሲ በቀጣይ የንግዱ ሕብረተሰብን እርስ በእርስ ለማገናኘት፣ የንግድ ለንግድ ግንኙነት የሚፈጠርበት በአጠቃለይ የግሉን ዘርፍ ለማሳደግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በኢትዮጵያና በቬንዝዌላ መካከል ያለው የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ገና ያልተነካ እና ብዙ እድሎች እንዳሉ በውይይቱ ላይ ተገልጿል ፡ ፡

ቬንዙዌላ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እያደረገች መሆኑ ለማወቅ ተችሏል ።

ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች በተለይም በግብርና ፣ በምግብ ማቀነባበር ፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሠማሩ በቬነዝዌላ በግልም ሆነ በሽርክና ኢንቨስትመንት መሠማራት የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸቱን አምባሳደሩ ጠቅሰዋል ።

ደቡብ አሜሪካዊቷ ቬንዙዌላ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኘነት 75 አመታትን አስቆጥሯል ።