የአዲስ ቻምበር ዝማሬ

በ1993 ዓም የተዘጋጀው እና ዘወትር የአዲስ ቻምበር የሬዲዮ ፕሮግራም መክፈቻ ሆኖ ሲያገለግል የቆየው እና በሕዝብ ጆሮ የተለመደው ‘ ራዕያችን’ የተሰኘው ዝማሬ መሠረቱን ሳይለቅ በተሻለ የድምጽ ጥራት እና ባማረ ሙዚቃዊ ቅንብር እንደገና ተዘጋጅቶና ተሻሽሎ በ75ኛ ዓመቱ ላይ አስመርቋል
***
ራእያችን
ራዕያችን…………………የዕድገት ጀምበር፣
መታወቂያችን………………..አዲስ ቼምበር፣
ቃል ኪዳናችን………..……..‘‘ይቻላል’’ ነው፣
የጥረት ውጤት………………..ፍሬ የሆነው
የኢኮኖሚ ጀርባ አጥንቶች……….የድንበሩ አጥሩ ምሶሶዎች
ለአዲስ ዕድገት ተጠባቢ………..የማንነጥፍ ያገር ሀብቶች፣
በ‘‘ይቻላል’’ መርሆአችን…………….ያገር ልጅን አስተባብረን፣
ለአዲስ ውበት ልምላሜ…………. ..የምንጥር ሣተኖች ነን።
የእኛ ጠላት ልመና ነው…………….እጅን መስጠት ለምፅዋት፣
ጥላችን ስንፍና ነው………………..………..ከእጅ ወደ አፍ ኑሮን መግፋት።
ይቻላል!!
የዕድገት ሳንካን ችግር መቅረፍ፣
ይቻላል!! ………………….…
የድኀነት ቅስምን መስበር፣
ይቻላል!! …………….………
ለክፉ ቀን ደራሽ መሆን፣
ይቻላል!! ……………….……
ፈጥኖ ማዳን የደከመን፣
አዝማች፡-
የዕድገት ውጥን ችግኞች ነን………ፀረ ድህነት አርበኞች፣
በአገር ፍቅር ተቃጣዮች……………ለችግር ፈጥኖ ደራሾች፣
በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ………………..የዜግነት ማተባችን፣
ኢትዮጵያችን ትድመቅ ትደግ……….እልፍ እንሁን በኀብረታችን።
የሰው ልጅ ዘር መገኛው መስክ……ለምለምና ውብ ቀዬዋ፣
ሠላም ይሁን አማን ይሁን……… ክቡር ይሁን ባንዲራዋ።