አዲስ ቻምበር ፤ጥቅምት 3 ቀን 2019፡ ስልጠናው በሥራ ፈጠራ፤በቢዝነስ አስተዳደር እና በንግድ እቅድ አዘገጃጀት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የሀብ ሊንክ ኮንሰልቲንግ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ገበያው ካሴ ሲሆኑ በአነስተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነጋዴዎች ስራቸውን በንግድ እቅድ አለመጀመራቸው በሚፈልጉት መጠን ውጤት እንዳያመጡ እንደሚደርጋቸው አስረድተዋል፡፡አክለውም ስራ ፈጣሪዎችም ሆኑ ሌሎች ነጋዴዎች ለገበያ ጥናት እና ለደንበኛ አያያዝ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
አዲስ ቻምበር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን የተለያየ የስልጠና መርሃግብር የሚያዘጋጅ ሲሆን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ነጋዴዎች የተሰጠው ስልጠና ከሳይፕ ( CIPE) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል፡፡
አዲስ ቻምበር የግሉ ዘርፍ ድምጽ!
