ታላቅ የንግድ እድል ለመላው የአዲስ አበባ የንግድ ማህበረሰብ፣ ከአንጋፋው አዲስ ቻምበር!!

አዲስ አበባ ታላቅ የቢዝነስ ፎረም እና የንግድ ለንግድ ውይይት ፕሮግራም ላይ እንድትሳፉ ስለመጋበዝ፤

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዱባይ ከሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ መሠረት የሀገራችንን በተለይም የአዲስ ቻምበር አባል ኩባንያዎች ከሻርጃህ ከተማ ጋር የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስርን ለማጠናከር የኤክስፖርት ፕሮሞሽን አጋርነትን የሚያበረታታ የሻርጃህ ከፍተኛ የቢዝነስ ልዑካን ቡድን እ.አ.አ. በኦክቶበር 2026 በሀገራችን(በአዲስ አበባ) የቢዝነስ ጉብኝት እና የአዲስ-ሻርጃህ የቢዝነስ ኮንፈረንስ እንደሚያደርግ ገልጾልናል፡፡

ስለሆነም ከሻርጃህ ባለሀብቶች ጋር የንግድ ትስስር ለመፍጠር እና በቢዝነስ ኮንፈረንሱ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱ ያላችሁ የንግድ ምክር ቤታችን አባል ኩባንያዎች ከታች በተመለከተው የምዝገባ ሊንክ መመዝገብ እንደምትችሉ የአዲስ ቻምበር የንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ መምሪያ ይገልጻል ።

👉🏻 የምዝገባ ሊንክ፡ https://forms.gle/6MsBWMwygzf4kTK5A

👉🏻 ለተጨማሪ መረጃ ዐ9111278ዐ7/ 0911212179/ ላይ መደወል ይችላሉ፡፡

አዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት፣ ላለፉት 80 አመታት የንግዱ ማህበረሰብ አገልጋይ እና ዋነኛ ድምፅ

#Addis chamber:Connecting Businesses since 1947