የንግዱ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!!
ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ ለምረቃ በመብቃቱ በመላው የንግዱ ማህበረሰብ ስም እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ የንግዱ ህብረተሰብ ከአነስተኛ እስከ ትልልቅ ኩባንያዎች ላበረከታችሁት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በዚች ታሪካዊ ወቅት በአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/አዲስ ቻምበር/ እና በራሴ ስም ታላቅ ምስጋና ይድረሳችሁ እላለሁ፡፤
ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ እና የሀይል ማመንጫ ለግሉ ዘርፍ ልማት አይነተኛ የመሰረተ ልማት አውታር መሆኑን እየገለጽኩ መላው ኢትዮጵያዊያን እና አጋሮቻችን እንኳን ደስ አላችሁ !!!!
ዘሐራ መሀመድ
ፕሬዚዳንት