ሁለቱ ተቋማት በተለይም ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ የአዲስ ቻምበር ፕረዚደንት ምክር ቤቱን በመወከል እንዲሁም ሚስተር ኢብራሂም ቡርካይ የቡርሳ ቻምበርን በመወከል ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡
ይህ ስምምነት የተፈረመው ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በተከፈተው በአዲስ ቻምበርና በቡርሳ የቢዝነስ ለቢዝነስ መድረክ ላይ ሲሆን ይህ የቢዝነስ መድረክ በቱርክ መንግስት፤ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ በአዲስ ቻምበርና በቡርሳ ቻምበር አማካኝነት በጋራ የተዘጋጀ መድረክ ነው፡፡
በዚህ ወሳኝ መድረክ ላይ ከ160 በላይ ግዙፍና ስመጥር የቱርክ ኩባያዎች፤ የቢዝነስ መሪዎች፤ ባለሀብቶችና አምራቾች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
