ሁለቱ ተቋማት በአዲስ ቻምበር በቅርቡ የተቋቋመውን የአረንጓዴ ልማትና ዘላቂነት ማእከልን ለማጠናከር ተስማምተዋል ።
በአዲስ ቻምበር ምክትል ዋና ፀሐፊዎች የተመራውን የማኔጅመንት እና የፕሮጀክት ሀላፊዎችን ተቀብለው ያነጋገሩት የአለምአቀፉ የአረንጓዴ ልማት ኢኒሼቲቭ (Global Green Growth Inititatives ) የኢትዮጵያ ሀላፊ ኦኬቹኩ ዳንኤል ኦግባናያ እና ሌሎች ሀላፊዎች ናቸው።
በውይይቱ የግሉ ዘርፍ በአረንጓዴ ቢዝነስ እና በዘላቂነት ላይ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ የተስማሙ ሲሆን በቅርቡ በአዲስ ቻምበር የተቋቋመውን እና ለንግዱ ማህበረሰብ ለማገልገል እውን የሆነውን የአረንጓዴ ልማት ማእከልን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
አለምአቀፉ ተቋም በተለያዩ መስኮች ከአዲስ ቻምበር ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል ።
አለምአቀፉ የአረንጓዴ ልማት ኢኒሼቲቭ ዋና መቀመጫውን ደቡብ ኮሪያ አድርጎ በተለያዩ ሀገራት ቢሮ ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
