አዲስ ቻምበር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ለሚገኙ አካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን የገና በዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ::

በከፍያለው ዋሲሁን

ንግድ ምክር ቤቱ በወረዳው ለሚገኙ ለ80 ያህል አካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን ለእያንዳንዳቸው 5 ሊትር ዘይትና 5 ኪሎ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል ፡፡

የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሽንቁጤ ምክር ቤታቸው የሰጠው ድጋፍ የተቸገሩና ደጋፊ የሌላቸውን የወረዳው ነዋሪዎች በዓሉን ደስ ብሏቸው እንዲያከብሩ የተደረገ ነው ብለዋል ፡፡

ምክር ቤታቸው የማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቁመው ፤ ሆኖም ድጋፍ በማድረግ ብቻ ችግሩን እንደማይቀረፍ ወ/ሮ መሰንበት ገልጸዋል ፡፡

ሁሌም ድጋፍና እርዳታ አይኖርም ያሉት ወ/ሮ መሰንበት ወደፊት ከእርዳታና ድጋፍ ወጥታችሁ ቋሚ ገቢ የምታገኙበት መንገድ ሊመቻች ይገባል ብለዋል ፡፡

በመሆኑም በችግር ውስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ከፍሎች በዘላቂነት ከችግር እንዲላቀቁ ፤ ንግድ ምክር ቤታቸው ከቂርቆስ ከፍለ ከተማ ጋር በቀጣይ እንደሚሰራ ጠቁመዋል ፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሰፋየ ነመራ በበኩላቸው በወረዳቸው ለሚገኙ ችግረኛ ወገኖች ንግድ ምክር ቤቱ ላደረገው ድጋፍ አመሰግነዋል ፡፡

አቶ ተሰፋየ አክለውም በወረዳቸው ለሚገኙ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች ንግድ ምክር ቤቱ ካለው በመቀነስ በድህነት ውስጥ የሚገኙ የህብረሰተብ ድጋፍ በወረዳቸው ስም ለንግድ ምክር ቤቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡