በአዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች አለም አቀፍ አውደ ርእዮችን ሊካሄድ መሆኑን የጀርመኑ አውደ ርእይ አዘጋጅ ኩባንያ Trade & Fairs Consulting GMBH አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች አለም አቀፍ አውደ ርእዮችን ሊካሄድ መሆኑን የጀርመኑ አውደ ርእይ አዘጋጅ ኩባንያ Trade & Fairs Consulting GMBH አስታወቀ፡፡
ኩባንያው በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽኖችን በተሳካ ሁኔታ በጋራ ለማካሄድ የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ከአዲስ ቻምበር ጋርም ተፈራርሟል፡፡ የጋራ መግባቢያ ሰነዱን የአዲስ ቻምበር ዋና ጸሃፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያምና የ Trade & Fairs Consulting GMBH ኩባንያ ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ስካንደር ፈርመዋል፡፡
አውደ ርእዮችን በተመለከተም በስካይ ላይት ሆቴል የጋራ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ መግለጫውንም የጀርመን ኤምባሲ፣የአፍሪካ ህብረት፣ የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ አዲስ ቻምበር ፣ Trade & Fairs Consulting GMBH ኩባንያ እና ታዋቂ ስራ ፈጣሪዎች በጋራ ሰጥተዋል።
በተያዘውም ሆነ በቀጣዮ በጀት አመት በሚካሄዱት የተለያዩ 4 አለም አቀፍ የንግድ ትርኢቶች ከብዙ ሀገራት የተውጣጡ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል፡፡