ላኪዎች የአሜሪካ ገበያዎችን መስፈርት በማሟሏት እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

አዲስ ቻምበር መስከረም 22 ቀን 2019 አ.ም፡- የኢትዮጵያ ሎጂስቲክስ ዘርፍ ማህበር ባዘጋጀው ሥልጠና ላይ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የሚላከው ወጪ ንግድ መጠን በየአመቱ ዕድገት ማሳየቱ ተነግሯል፡፡ እ.ኤ.አ በ2024 ወደ አሜሪካ ከተላከው ወጪ ንግድ  466 ሚልየን ዶላር፤በ2025 ደግሞ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ መገኘቱን አስታውሰው ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ብቻ 1 ቢሊየን ዶላር መገኘቱን    የማህበሩ ፕሬዝደንት ወ/ሮ ኤልሣቤት ጌታሁን አስታውቀዋል፡፡

ስለጠናውን በበይነመረብ የሰጡት ወ/ሮ ሰላማዊት ሰይፉ  አብዛኞቹ የአገራችን ላኪዎች ለአሜካን ገበያዎች የሚያቀርቡት ምርትና አገልግሎቶች በጥራትና በአይነት ተወዳዳሪ መሆናቸውን ግልጸዋል፡፡  ነገር ግን ከአሜሪካ የወጪ ንግድ መመሪያዎች ፤ የጥራትና የደረጃ መስፈርቶች፤ የማሸጊያ እና የይዘት መረጃ አሰጣጥ ላይ  ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ በተለይ በታሸጉ ምግቦች፤አለባሳት እና የእንጨት ውጤቶች ላይ ከጤና ጋር በተያያዘ በአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ በእነዚህ እና በሌሎች ምክንቶች በርካታ ላኪዎች ችግር ይገጥማቸዋል፡፡

ከኢትዮጰያ ወጪ ምርቶች  ከመዳረሻቸው የሚደርሱት ከ 15 በላይ የሚሆን ተቋማትን ይሁንታ ማገኘት አለባቸው፡፡   እንደ  አትክልትና ፍራፍሬ የመሳሰሉ በቶሎ የሚበላሹ ምርቶች እንደ ሰርቲፊኬት ኦፍ ኦሪጂን እና  ከጤናና አካባቢ ጋር የተያያዙ  የኤክስፖርት ሰነዶችን ከመላኪያ ቀናት በፊት አስቀድሞ ማጠናቀቅ  እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

አንድ ላኪ ወደ አሜሪካ ገበያ ለመግባት ማሟላት ያለበትን የጥራት፤የደረጃ እና የብቃት መለኪያዎችን በዝርዝር ያብራሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ላኪዎች ከምንጊዜውም በላይ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምርቶች  በማቅረብ ከሰፊው የአሜሪካ ገበያ ዕድል እንዲጠቀሙ ጥዕሪ አቅርበዋል፡፡  በስልጠናው ላይ ከተሳተፉ ላኪዎች ለተነሱት በርካታ ጥያቄዎች ወ/ሮ ሰላማዊት ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አዲስ ቻምበር የግሉ ዘርፍ ድምጽ!