ለግሉ ዘርፍ የቀረበው ብደር መጠን ጭማሪ አሳየ፤ ለአነ/መካ/ኤንተርፕራይዞች ደግሞ እጥፍ መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለግሉ ዘርፍ የቀረበው ብደር መጠን ጭማሪ አሳየ፤ ለአነ/መካ/ኤንተርፕራይዞች ደግሞ እጥፍ መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አዲስ ቻምበር ሚያዝያ 28 ቀን 2018 አ.ም፡- የገንዘብ ሚኒስቴር የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ከተጀመረ ወዲህ የተከናወኑ ሥራዎችና የተገኙ ወጤቶችን አሰመልክቶ የ18 ወራት መዘርዝር (ሪፖርት) አውጥቷል፡፡ በመዘርዝሩ ላይ ከተመለከቱ ዋና ዋና ከንውኖች መካከል ለግሉ ዘርፍ የቀረበው የብድር መጠን ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ አንዱ ነው፡፡

 

በዚህ መሠረት ባንኮች ያቀረቡት የብድር መጠን 23 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 77 በመቶ የሚሆነው ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ ነው፡፡ ይህም በአኃዝ ሲገለጽ ወደ 823 ቢሊየን ብር መሆኑ መዘርዝሩ ያትታል፡፡

 

በተመሳሳይ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የተሰጠው የብድር መጠን እንዲሁ በከፍተኛ ደረጃ ዕድገት አሳይቷል፡፡ ከ2 አመት በፊት ለአነ/መካ/ኢንተፕራይዝ አንቀሳቃሾች የተሰጠው የብደር መጠን 84 ቢሊየን ብር የነበረ ሲሆን በእነዚህ ወራት ወሰጥ 167 ቢሊየን ብር መድረሱ ተመልክቷል ፡፡ በባንኮች ዘንድ የሚገኘው የተበላሸ ብድር ምጣኔ 3 በመቶ ላይ መጠበቅ መቻሉንም ከመዘርዝሩ ለመረዳት ተችሏል፡፡

 

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ንግድ ም/ቤት (አዲስ ቻምበር) መጋቢት 3 2018 አ.ም ባዘጋጀው የግሉና የመንግስት የምክክር መድረክ ላይ ከተሰነዘሩት ምክረ ሃሳቦች መካከል ባንኮች የሚሰጡት የብድር መጠን ጣሪያ 18 በመቶ እንዳይበልጥ የሚያዘው የብሔራዊ ባንክ መመሪያ የንግዱን ሕ/ሰብ እንቅስቃሴ ከሚያቅቡ ተግዳሮቶች መካከል አንዱ መሆኑ የተወሳ ሲሆን ብሄራዊ ባንክ መመሪያውን እንዲያነሳ የሚጠይቅ ምክረ ሃሳብ ከግሉ ዘርፍ ተሰንዝሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

wpChatIcon
wpChatIcon