የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በአለም አቀፍ ንግድ ላይ የተሠማሩ አባላቱ የሚገጥማቸውን ችግር ያቃልላል ያለውን የዲጂታል ስርዓት ( export portal) ይፋ አደረገ።

የዲጂታል ስርዓቱ በአለም አቀፍ ንግድ ለተሰማሩ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የገበያ መዳረሻዎችን እና ህጎችን የተመለከቱ መረጃዎችን የሚሰጥ መሆኑ ተጠቅሷል።