የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ከሮሜንያ የመጡ ባለሃብቶችን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሃራ መሐመድ ከቦርድ አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን ቆሻሻን ወደ ዘላቂ ሃይል መቀየር የሚያስችል ግዙፍ ቴክኖሎጂን ይዘው ከመጡ የሮሜንያ ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል ፡፡

ባለሃብቶቹ ቴክኖሎጂው ማንኛውንም ቆሻሻ ወደ ሃይል በመቀየር ከአየር ብክለት የጸዳ እና ዘላቂ የሆነ የሃይል አቅርቦት ማስገኘት እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

አክለውም ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ቴክኖሎጂአቸውን ለማስተዋወቅ እና ከሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ጋር የንግድ ግንኙነት ለመፍጠር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የተገኙት የምክር ቤቱ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር መሰረት ሞላ ንግድ ምክር ቤቱ ለንግዱ ማህበረሰብ አለም አቀፍ የንግድ ግንኙነት እድሎችን ከመፍጠር እና ከማመቻቸት ባለፈ ሌሎች አገልግሎቶቹን አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም ባለሃብቶቹ አዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ከሚሰጠው አገልግሎት አንጻር በምን መልኩ ሊያግዛቸው እንደሚችል በጠየቁት መሰረት የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሃራ መሃመድ ምክር ቤታቸው ማንኛውንም ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

የሮሜኒያ ባለሀብቶች በኢትዬጲያ መዋእለነዋዬቻቸውን እንዲያፈሱም አዲስ ቻምበር ጥሪ አቅርቧል ።

wpChatIcon
wpChatIcon