የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ከ1000 በላይ ለሚሆኑ አረጋውያን የኢፍጣር መርሐ-ግብር በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል በመገኘት አካሄዱ።

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት(አዲስ ቻምበር) ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሐመድ እና የቦርድ አባላት የረመዷንን ጾም ምክንያት በማድረግ ከ 1000 በላይ ለሆኑ አረጋውያን የኢፍጣር መርሐ-ግብር በመቄዶንያ አካሂደዋል ፡፡

ፕሬዝዳንቷ እንደገለፁት አዲስ ቻምበርም ሆነ መላው የንግዱ ሕብረተሰብ በተለያየ መልኩ ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በቻለው አቅም ከጎን በመሆን ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን አጠናክረው እንዲወጡ አሳስበዋል ።

በኢፍጣሩ  ላይ የተገኙት የማእከሉ መስራች አቶ ቢኒያም በለጠ ለምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት በአረጋዊያን እና በህሙማኑ ስም ምስጋና አቅርበው አዲስ ቻምበር እና አባላቱ ባለሀብቶች እንዲህ ያለውን የማህበራዊ ሀላፊነት የመወጣት ስራ በዘላቂነት እንዲወጡ በአክብሮት ጥሪ አቅርበዋል ።

wpChatIcon
wpChatIcon