የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር/ የሰራተኞች መረዳጃ ማህበር ተቋቋመ ፡፡ የማህበሩ መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብም ለሰራተኞች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ማህበሩን የሚመሩ 5 የስራ አስጻሚዎች ምርጫም ተካሂዷል፡፡
ማህበሩ በምክር ቤቱ ሠራተኞች መካከል የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍ፣ የመቀራረብ፣ የመረዳዳትና ቤተሰባዊ መንፈስ በማዳበር የሠራተኛውን ማህበራዊ ግንኙነት በበበለጠና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ለማጠናከር ታስቦ የተቋቋመ መሆኑም ተመላክቷል።
የማህበሩም ደንብ እንደሚያስረዳው አባል ለመሆን ማንኛውም ፈቃደኛ የሆነ/ች የአዲሰ ቻምበር ቋሚም ሆነ ኮንትራት ሰራተኛን የሚያካትት እንደሆነ ነው ፡።
መረዳጃ ማህበሩ እንዲቋቋም ረቂቅ ሰነድ ላቀረቡ 5 የኮሚቴ አባላትም የምክር ቤቱ ዋና ጸሃፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያም በእርሳቸውና በመላው ሰራተኛ ስም ምስጋና አቅርበውላቸዋል፡፡