(ጥቅምት 29፣2015 ) ሰባት አባላት ያሉት የአሰላ ንግድ ምክር ቤት የቦርድ አባላት ከአዲስ ቻምበር ዋና ጸሃፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያምና የፅህፈት ቤቱ የማኔጅመንት አባላት ጋር በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል ፡፡
የአዲስ ቻምበር ዋና ጸኃፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያም በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት የአሰላ ንግድ ምክር ቤት እንዲጠናከር ንግድ ምክር ቤታቸው አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ ያደረጋል ብለዋል ፡፡
በተለይም በፕሮጀክት ቀረፃ ፣ በስልጠናና አቅም ግንባታ ፣ በንግድ ትርኢት አዘገጃጀት እና ጽ/ቤትን በማጠናከር ዙሪያ ከአሰላ ንግድ ምክር ቤት ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል ፡፡
የአሰላ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራሮች በበኩላቸው አባላትን በማፍራት ፣ የገቢ ምንጭን በማሳደግና ፕሮጀክትን በመቅረፅ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ረገድ የአዲስ ቻምበርን ተሞክሮ ለቀጣይ ስራቸው እንደሚጠቀሙበት አመልክተዋል ፡፡