የሳውዲ አረቢያው ኔት ገልፍ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጅ ኩባንያ በዘርፉ ከሚሰሩ የአዲስ ቻምበር አባላት ጋር በጋራ መሰራት በሚችልበት ሁኔታ ላይ መከረ ፡፡

የሳውዲ አረቢያው ኔት ገልፍ የአይቲ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚሰተር አህመድ ያህያ በአዲስ ቻምበር በመገኘት በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ፣ በእውቀት ሽግግርና በትብብር መሰራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል ፡፡
ኩባንያቸው ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ዘርፍ ከተሰማሩ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር በትስስርና ትብብር ለመስራት መሆኑንም ሚሰተር አህመድ ገልፀዋል ፡፡
የአዲስ ቻምበር ዋና ፀሀፊ አቶ ሺበሺ ቤተ ማርያም በበኩላቸው ሁለቱ አገራት ያላቸው ግንኙነት ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በንግድና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡
የሳውዲ አረቢያው ኔትገልፍ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅና ቴሌኮም ኩባንያ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ደግሞ በንግድ ላይ ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን ያላቸውን እምነት ገልፀዋል ፡፡
የሳውዲው ኩባንያ ስራ አስፈጻሚ እንደተናገሩት ወደ ኢትዮጵያ የምንመጣው ከኢትዮጵያዊያን ኩባንያዎች ጋር ያለውን ገበያ ለመሻመት ሳይሆን ትስስር እና አጋርነት ፈጥረን በጋራ መስራት እንፈልጋለን ብለዋል ፡፡
አክለውም ያላቸውን ልምድ በቴክኖሎጅው ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች የመደገፍና ለችግሮችም መፍትሄ የመሰጠት ስራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል ፡፡
በውይይቱ ላይ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አራት አገር በቀል ኩባንያዎችም ሰለድርጅቶቻቸውና ዘርፉ በሀገሪቱ ስላለበት ደረጃ ለኔት ገልፍ አመራሮች ገለፃ አድርገውላቸዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *