አዲስ ቻምበር 16ኛውን ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በኢንተር-ሌግዠሪ ሆቴል (በቀድሞው ኢንተርኮንትኔታል ሆቴል) ሐሙስ፣ መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ያካሂዳል፡፡

ጉባኤው የ2012፤የ2013 እና የ2014 በጀት ዓመት የሥራ ክንውንን ይገመግማል፡፡ የውጭ ኦዲተሮች የሚያቀርቡትን ሪፖርት መርምሮ ያፀድቃል፤ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት፣ ም/ፕሬዚዳንትና የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫም ያከናውናል፡፡

ጉባኤው የንግዱን ኅብረተሰብ መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚያስችሉ ሀሳቦች የሚፈልቁበት መድረክ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *