የኢትዮጵያና የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰበት የአፋር ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ ፡፡

ሁለቱ ንግድ ምክር ቤቶች 42 ወንበሮች፣ 9 ጠረጴዛ ፣ 4 ዴስክቶፕ ፣ 1 ላፕቶፕ ኮምፒዊተሮችን በጋራ አበርክተዋል፡፡

የአፋር ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተወካይ አቶ ከበደ መሀመድ ድጋፉን ሲከረቡ አንዳሉት በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው ከተዘጉ ተቋማት አንዱ ንግድ ምክር ቤታቸው መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

በመሆኑም የተደረገው ድጋፍ ንግድ ምክር ቤቱን ዳግም ወደነበረበት እንዲመለስ የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሰው ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ተወካይ አቶ ሚሊዮን ፈለቀ በርክክብ ሰነ ሰርዓቱ ውቅት እንዳሉት በግጭቱ ጉዳት ለደረሰበት ለአፋር ንግድ ምክር ቤት የተደረገው ድጋፍ በቂ አይደለም ብለዋል ፡፡

በመሆኑም በቀጣይ ከዚህ የበለጡ መሰል ድጋፎችን ምክር ቤታቸው እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የስው ሃብትና ሎጀስቲክስ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ናርዶስ አማረ በበኩላቸው ድጋፉ የመጀመሪያ እንጅ የመጨረሻ አለመሆኑን ተናግዋል ፡፡
በቀጣይም በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸውና በምስራቅ አማራ ለሚገኙ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች መስል ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል ፡፡

የአዲስ አባባ ንግድ ምክር ቤቱ ከቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ የአቅም ግንባታ ስልጠናና የቴክኒክ ድጋፎችን እናደርጋለን ብለዋል ፡፡