አዲስ ቻምበር ለአማራ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ልምድና ተሞክሮውን አካፈለ ፡፡

በአማራ ክልል ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት የተመራ የቦርድ አባላትንና የክልሉ ንግድና ልማት ቢሮ አባላትን ያካተተ ሉዕክ በንግድ ምክር ቤቱ በመገኝት ልምድ ቀስሟል ፡፡
በዚህም ንግድ ምክር ቤቱ ስላለው አደረጃጀት እና የእያንዳንዱ ክፍል ስራን እንዲሁም አጠቃላይ የምክር ቤቱን እንቅሰቃሴ በተመለከተ ም/ዋና ፀሀፊ አቶ ዘካሪያስ አሰፋ ገለፃ አድርገዋል ፡፡
የአዲስ ቻምበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ፋሲካው ሲሳይ ሉዕካኑ ወደ ንግድ ምክር ቤቱ መጥተው ልምድ መቅሰማቸው በሀገራችን ሊዳብር የሚገባ ባህል መሆን አለበት ብለዋል ፡፡
አዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 78 ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ ንግድ ምክር ቤት መሆኑንና 17 ሺ አባላት ያሉት መሆኑን ገልፀው የሀገሪቱ 60 በመቶ ጥቅል አመታዊ ምርት የሚሽፍነው የግሉን ዘርፍ የያዘች ከተማ ንግድ ምክር ቤት በመሆኑ ንግድ ምክር ቤቶች እርስ በእርስ ለመደጋገፍ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ምንም እንኳን የክልልና የከተማ ንግድ ምክርቤቶች እየተባልን ብንስራም አላማችን የግሉን ዘርፍ መደገፍ ነው ብለዋል::
የአዲስ ቻምበር አደረጃጀት ምን ይመሰላል የሚለውን ገለፃ ከተደረገላቸው በኃላ የዐማራ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጥያቄዎችን እንዲሁም ሰለ አዲስ ቻምበር አደረጃጃት የተሰማቸውን አድናቆት ገልፀዋል ፡፡
የልምድ ልውውጥ መልካም ቢሆንም እርስ በእርስ ልምድን መካፍል ላይ ውሰንነቶች አሉ ያሉት የዐማራ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አባላት ፤ ወደ አዲስ ቻምበር የመጣነው ያለንን አሰራር ለማዳበር የሚያስችል በቂልምድና ተሞክሮ ለመውሰድ ነው ብለዋል ፡፡
በተለይ ከግልግል ዳኝነት ፣ አባላት ጉዳዮችና ፣ የዳሬክቶሮች ኢንስቲትዩት ኃላፊዎች ምክር ቤቱ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ለቀጣይ ሰራቸው የሚሆን ገንቢ ትምህርት ወሰደናል ብለዋል፡፡
በዚህም አዲስ ቻምበር አገሪቱን የሚወክል ጠንካራ ንግድ ምክር ቤት ሆኖ እንዳገኙት ነው የተናገሩት ፡፡
በንግድ ምክር ቤቱ ውስጥ ያለው አደረጃጀት እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችና በውስጡ ያሉት ባለሙያዎች እናዳሰደነቃቸው ጠቅሰው ይህንን አሰራር በዐማራ ንግድ ምክር ቤት ለመተግበር አዲስ ቻምበርን እገዛ ጠይቀዋል፡፡
ንግድ ምክር ቤቱ አሁን ላይ ታሪካዊ እና ሰር ነቀል ሪፎርም በማድረግ ላይ መሆኑን ለሉዕካኑ አባላት ገልፀው በቀጣይ አብረን እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል ፡፡
አዲስ ቻምበር ከሳምንታት በፊት ለሸገር ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ልምዱን ማካፈሉ ይታወሳል፡፡