ንግድ ም/ቤቱ በዲጂታል  ግብይት ሥርዓት ላይ ሥልጠና ሰጠ

ንግድ ም/ቤቱ ያዘጋጀው ሥልጠና  አባላቱ እና የውስጥ ሠራተኞች በዲጂታል ግብይት ላይ በቂ ግንዛቤ በማስጨበጥ የም/ቤቱን አገልግሎት ለማሻሻል ፤ እንዲሁም አባል ኩባያዎችን  ከዘመናዊው የዓለም ዲጂታል  የቢዝነስ ሥርዓት ጋር አብሮ እንጓዙ ለማገዝ  ታስቦ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የዲጂታል ግብይት ሥርዓት ከተለመደው የሬዲዮ፤የቴሌቪዥን እና የሕትመት ዘዴዎች በይበልጥ ፈጣን ፤አነስተኛ ጊዜ፤ ወጪ እና ጉልበት የሚጠይቅ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ በቅጽበት ተደራሽ የሆነ የግብይት ስልት ነው፡፡

አንድ ነጋዴ በዚህ በፈጣን እና ውድድር በበዛበት ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንደሆን ከተፈለገ በቀላሉ ሲፈለግ የሚገኝ ድረገጽ፤ኢ-ሜይል፤ማሕበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም የግድ እየሆነ መምጣቱንም ስልጠናውን የሰጡት ወ/ት ሃና ገበየሁ ተናግረዋል፡፡

በአገራችን የዲጂታል ግብትይ ባሕል በሕብረተሰቡ ዘንድ እየተለመደ  እያደገ በመምጣት ላይ ነው፡፡

በማሕበራዊ የትስስር ሚዲያዎች ማካኝነት የዲጂታል ግብይቶች በእጅ ስልክ ላይ ማከናወን እየተለመደ መጥቷል ሲሉ ሌላው አሰልጣኝ አቶ ሚካኤል በቀለ ተናግረዋል፡፡

በመንግሥትም በኩል   የንግድ ምዝገባ እና ዕድሳት እና መሰል አዳዲስ አሰራሮች መዘርጋታቸው  አንዲሁም የዲጂታል ክፍያ ፤የኤክትሮኒክ  ደረሰኝ እና ፊርማ የመሳሉት ሕግጋት መዘጋጀታቸው የዲጂታል ምሕዳሩን የሚያበረታቱ እንደሆኑ አቶ ሚካኤል ገልጸው  ነገር ግን ከሌሎች አገራት ከደረሱበት ደረጃ ሲነጻጸር ብዙ  ይቀረናል  ብለዋል፡፡

የዲጂታል ማርኬቲንግ ሌላው ገጽታ  የግዢ ትዕዛ እና ክፍያዎችን  በቀላሉ ማከናወን የሚያስችል በመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል ፡