በአዲስ ቻምበርና በ SAK የስልጠናና ማማከር ተቋም በየወሩ በጋራ የሚዘጋጀው የስራ መሪዎች መድረክ ተካሄደ ፡፡

በአዲስ ቻምበርና በ SAK የስልጠናና ማማከር ተቋም በየወሩ በጋራ የሚዘጋጀው የስራ መሪዎች መድረክ ተካሄደ ፡፡
በከፍያለው ዋሲሁን
በእለቱ ተጋባዥ እንግዳ በመሆን የቀረቡት የአዲስ ቻምበር እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቀድሞ ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉት አሁን ላይ የፓን አፍሪካ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የኢንሼቲቭ አፍሪካ ዋና ዳሬክተር አቶ ክቡር ገና ለአመታት ያካበቱትን ልምድና ተሞክሯቸውን ለኩባንያ አመራሮች አካፍለዋል፡፡
መሪ ማለት የሕዝብ አገልጋይ እና እራሱን የሆነ ፣ ማድመጥ የሚችልና ውጤት ተኮር ስራ የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
አንድ መሪ ጥሩ መሪ ነው የሚባለው ሌሎችን ወደ መሪነት እንዲመጡ ሲደግፍ ፣ ከተከታዪቹ ጋር አብሮ መራመድ ሲችል መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል ፡፡
አንድ መሪ ፤ መሪ ነው የሚባለው ለሚሰራው ስራ ኃላፊነት የሚወስድ እና እሰከመጨረሻው ተከታትሎ ከግብ ማድረስ የሚችል ጭምር ነው ብለዋል ፡፡
አንድ ተቋምን የሚመራ መሪ ለአንድ አላማ ሌሎችን የሚያሰባሰብ ፣ ሃሳባቸውን የሚቀበልና አሳታፊ ሆኖ የሚሰራ ከሆነ ውጤታማነቱ የተረጋገጠ መሆኑን ጠቅሰው ፤ ከዚህ በተቃራኒው ከሆነ ውጤቱ ውድቀት መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
በመሆኑም መሪ አርቆ ማየትና መገመት አለበት ብለዋል።
መሪዎች ችግር ሲገጥማቸው የማይናወጡ እና የማይጨነቁ ብሎም እንዴት እንፍታው ብለው መፍትሄ የሚፍለጉ እነሱ መሪዎች ናቸው ብለዋል ፡፡
በኢንተር ላግዥሪ ሆቴል በተካሄደው የስራ መሪዎች መድረክ ከሰማኒያ በላይ የኩባንያ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።