ስልጠናው በቻይና ኤምባሲ፣ በቤጂንግ የአለም አቀፍ ግንኙነት ጥናት ዩኒቨርስቲ እና በአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት(አዲስ ቻምበር)ና በሌሎች ባለድርሻ አካላት በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
ሥልጠናው የሴቶችን የቢዝነስ አመራር አቅምን ለማሳደግ ያለመ የቻይና ዓለም አቀፍ ኢንሼቲቭ አካል ነው።
ለሁለት ሳምንት በቆየው ስልጠና 60 በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሠማሩ ኢትዬጲያውያን ነጋዴ ሴቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
አዲስ ቻምበር በርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ በሴቶች የሚመሩ እና የተመሠረቱ ኩባንያዎችን በአባልነት አቅፎ የተለያዩ የንግድ አገልግሎቶችን እየሠጠ ይገኛል።
#አዲስቻምበር ፤ ለ78 አመታት የንግዱ ማህበረሰብ አገልጋይ
