ውይይቱ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ በሚካሄደው የንግድ ከንግድ ውይይት(B2B) ላይ ትኩረት ያረገ ነው፡፡
በውይይቱ የምክር ቤቱ ዋና ጸሃፊ አቶ ዘካርያ አሰፋ ለተሳታፊዎች የንግድ ምክር ቤቱን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከቻይና በኩል በውይይቱ የተሳተፉት ከንግድ ልማት ቢሮ እና ከውጭ ንግድ መምሪያ እንዲሁም የቻይና ኢንባሲ ተወካዮች ጥያቄዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡
ነሐሴ 13 ቀን 2018 የሚካሄደው የንግድ ከንግድ ውይይትም ለሃገር ውስጥ ነጋዴዎች ከቻይና ገበያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለቻይና ኩባንያች ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲያስሱ እንደሚያስችላቸው ተጠቅሷል፡፡
