የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ባዘጋጀው የቢዝነስ ሴሚናር ላይ 300 የሚጠጉ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት አባላትና አቅራቢዎች ተሳትፈዋል ፡፡
የአዲስ ቻምበር ተ/ዋና ፀሐፊ አቶ ዘካሪያስ አሰፋ በሴሚናሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት የተባበሩት መንግስታት በሚያወጣቸው የአገልግሎትና የእቃዎች ግዢና ጨረታ የከተማይቱ የንግድ ህብረተሰብ ይበልጥ ተሳታፊ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን አዲስ ቻምበር አበክሮ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
የንግዱ ሕብረተሰብም ተወዳዳሪ እንዲሆን የአቅም ግንባታ ስራዎች ምክር ቤቱ ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን ያከናወናል ብለዋል።
አዲስ ቻምበር በኮሚሽኑም ሆነ በሌሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች የሚወጡ የግዢ ፍላጎቶች መላው የንግዱ ህብረተሰብ ተሳታፊና አቅራቢ የሚሆንበትን ሁኔታ እንፈጥራለን ብለዋል ፡፡
እንዲህ ያሉ የንግድ እድሎችን ለመላዉ የንግዱ ሕብረተሰብ በማቅረብ ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ባዘጋጀው በዚህ የቢዝነስ ኮንፈንስ ላይ የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት ሀላፊዎች እና ተወካዬች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መልእክት አስተላልፈዋል ፡ ፡
በኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ስር የሚንቀሳቀሱ 29 ተቋማት እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ ።
በአዲስ አበባ ብቻ በተለያዩ የንግድ መስኮች የተሰማሩ ከ480 ሺሕ በላይ የንግድ ፈቃድ ያወጡ ነጋዴዎች ይገኛሉ።
አዲስ አበባ ቻምበር እና የተመድ የአፍሪቃ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አጋርነት ረዥም አመታትን አስቆጥሯል ።